Entries by media

እስመ ናሁ ተወልደ ለክሙ ዮም መድኅን ዘውእቱ ክርስቶስ እግዚእ ቡሩክ በሀገረ ዳዊት

“እስመ ናሁ ተወልደ ለክሙ ዮም መድኅን ዘውእቱ ክርስቶስ እግዚእ ቡሩክ በሀገረ ዳዊት ፥ እነሆ ዛሬ በዳዊት ሀገር መድኅን ተወልዶላችኋል፤ ይኸውም ቡሩክ አምላክ ክርስቶስ ነው።” ሉቃ ፪ ፥ ፲፩ ለመላው የክርስትና ሃይማኖት ተከታዮች ካህናት፣ ዲያቆናት፣ ምእመናንና ምእመናት በሙሉ፤ ዓለሙን ሁሉ ፈጥሮ የሚገዛ ለቸርነቱ ወሰን የሌለው አምላካችን እንኳን በሰላምና በጤና ጠብቆ ለበዓለ ልደቱ አደረሳችሁ ፥ አደረሰን። በዓሉ የሰላምና […]

የምሥራቅ፣ ምዕራብና ደቡብ አውሮፓ ሀገረ ስብከት የ፳፻፱ ዓ/ም የሥራ ክንውን ዘገባ

እንደሚታወቀው ፳፻፱ ዓ/ም የሥራ ዘመን በሀገረ ስብከታችን ታሪክ በልዩ ሁኔታ ሲዘከር የሚኖር የሥራ ዘመን ነው። ልዩ የሚያደርገውም ቀደም ሲል በሀገረ ስብከቱ ውስጥ በልዩ ልዩ ኃላፊነት በማገልገል ላይ ከሚገኙት አባቶች መካከል እንደአገልግሎት ዘመናቸውና እንደ አገልግሎት ፍሬያቸው ቅድሚያ ተሰጥቷቸው ትምህርታቸውንና አገልግሎታቸውን በዝርዝር የሚያስረዳ ሰነድ አዘጋጅቶ ለኤጲስ ቆጶስነት ምርጫ በእጩነት ካቀረባቸው ፮ አባቶች መካከል ፫ቱ የቅዱስ ሲኖዶስን ይሁንታ […]

“ተፋቀሩ ዘልፈ እስመ ማእሠረ ተፍጻሜቱ ውእቱ — ዘወትር በፍቅር ኑሩ የመጨረሻው ማሠሪያ እሱ ነውና።” ቆላ ፫፥፲፬

የብፁዕ አቡነ ሙሴ የቅዱስ ሲኖዶስ አባል እና የመላው አውሮፓ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ቃለ ምዕዳን መስከረም ፳፻፲ ዓ/ም በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። የተከበራችሁ የአድባራት አስተዳዳሪዎች፣ ካህናት፣ ዲያቆናት፣ ምእመናንና ምእመናት እንዲሁም የሰ/ት/ቤት ወጣት መዘምራን መዘምራት፥ ቸርነት የባሕርይ ገንዘቡ የሆነ የዕለታትና የዓመታት የጊዜያት ሁሉ ባለቤት በአንድነት በሦስትነት ሲመሰገን የሚኖር አምላካችን እንኳን ሁላችንንም በሰላምና በጤና […]

የብፁዕ አቡነ ሙሴ ቃለ ምእዳን ፳፻፱ ዓ/ም

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! የተወደዳችሁ አዕይንት እግዚአብሔር ካህናት እና አባግዐ ክርስቶስ ምእመናን፤ ቸርነት የባሕርይ ገንዘቡ የሆነ አምላካችን እግዚአብሔር እንኳን በሰላምና በጤና ጠብቆ ከዘመነ ዮሐንስ ወደ ዘመነ ማቴዎስ አሸጋገራችሁ፤ አዲሱ ዘመን የሰላምና የበረከት ዘመን ይሁንላችሁ። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ “እንከሰ ጽንዑ በእግዚአብሔር ወበጽንዐ ኃይሉ ወልበሱ ወልታ እግዚአብሔር በዘትክሉ ተቃውሞቶ ለመናስግተ ሰይጣን“ ትርጉም “ከእንግዲህስ […]

በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የምሥራቅ፣ ምዕራብና ደቡብ አውሮፓ ሀገረ ስብከት የ፳፻፯ ዓ/ም የሥራና አገልግሎት ዘመን ዓመታዊ ሪፖርት

ሀገረ ስብከቱ በአዲስ መልክ ተዋቅሮ ሥራውን ከጀመረ ወዲህ ፳፻፯ ዓ/ም ፪ኛው የሥራ ዘመን ሲሆን በሥራ ዘመኑ ሀገረ ስብከቱን ከማደራጀት ጎን ለጎን የተቋቋመበትን መንፈሳዊ ተልዕኮ በአግባቡ በመወጣት በሥሩ ለሚያስተዳድራቸው አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናትናትና ለሕዝበ ክርስቲያኑ አልፎ ተርፎም ለመላዋ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሁለንተናዊ ዕድገት የበኩሉን አስተዋጽኦ ለማበርከት አቅምና ሁኔታ በፈቀደው መጠን የሥራና የአገልግሎት መሰናክል የሆኑ ሁኔታዎችን […]

የ፳፻፱ ዓ.ም በዓለ ልደትን በማስመልከት ቅዱስ ፓትርያርኩ የሰጡት ቃለ ምዕዳን

ቃለ በረከት ዘብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በእንተ በዓለ ልደቱ ለእግዚእነ ወአምላክነ ወመድኃኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ ሎቱ ስብሐት!! በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!! በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፤ ከሀገር ውጪ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፤ የሀገራችንን ዳር ድንበር ለመጠበቅና ለማስከበር በየጠረፉ የቆማችሁ፤ […]

የብፁዕ አቡነ ሙሴ ቃለ ምእዳን ፳፻፰ ዓ/ም

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! በቅርብም በሩቅም ያላችሁ ሕዝበ ክርስቲያን የመንፈስ ልጆቼ ቸርነት የባሕርይ ገንዘቡ የሆነ አምላካችን እግዚአብሔር አምላክ እንኳን ከዘመነ ሉቃስ ወደ ዘመነ ዮሐንስ በሰላም አደረሳችሁ፤ አዲሱን ዘመን የሰላም የበረከትና የጤና ዘመን ያድርግልን። እንደ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ ዘመን ከአራት ይከፈላል፥ ከመስከረም ፳፮ እስከ ታኅሳስ ፳፭ የነፋስ ወራት፣ ከታኅሳስ ፳፮ እስከ መጋቢት […]

በሀገረ ስብከቱ ያሉ አጥቢያዎች

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በደቡብ፣ ምሥራቅ እና ምዕራብ አውሮፓ ሀገረ ስብከት ሥራ ያሉ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት መረጃዎች (ስም፣ አድራሻ፣ ድረገጽ እና የመሳሰሉት) ይቀመጥበታል።

አስተርእዮተ እግዚአብሔር በደብረ ታቦር

‹‹አስተርእዮ›› ሥርወ ቃሉ ‹‹አስተርአየ (አርአየ) = አሳየ፣ ገለጠ፣ ታየ፣ ተገለጠ›› የሚለው የግእዝ ግስ ሲኾን ትርጕሙም ‹‹መታየት፣ መገለጥ፣ ማሳየት፣ መግለጥ›› ማለት ነው /ኪዳነ ወልድ ክፍሌ/፡፡ ‹‹አስተርእዮተ እግዚአብሔር በደብረ ታቦር›› የሚለው ሐረግም ‹‹የእግዚአብሔር በታቦር ተራራ መገለጥ›› ወይም መታየት የሚል ትርጕም ያለው ሲኾን